am_tn/deu/12/05.md

1.3 KiB

አምላካችሁ እግዚአብሔር ስሙን ሊያስቀምጥበት ከነገዶቻችሁ ሁሉ የሚመርጠው ስፍራ

እዚህ ጋ “ስሙን” የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ራሱን ነው። እግዚአብሔር የሚኖርበትን አንድ ቦታ ይመርጣል፣ ሰዎች እርሱን ለማምለክ ወደዚያ ይመጣሉ። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

መሄድ የሚኖርባችሁ ወደዚያ ነው

እግዚአብሔር ወደሚወስነው ስፍራ ለማምለክ ይሄዳሉ

በእጃችሁ የምታቀርቡት ስጦታ

እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ሙሉ ሰውነትን ነው። አ.ት፡ “የምታቀርቡት ስጦታ” (See: Synecdoche)

የስእለቶቻችሁንና የፈቃደኝነት ስጦታዎቻችሁን

“ስእለታችሁን የምትፈጽሙበትን ስጦታዎቻችሁን፣ የበጎ ፈቃድ ስጦታዎቻችሁን”። እነዚህ የስጦታ ዓይነቶች ናቸው።

ከቀንድ ከብቶቻችሁና ከበግና ከፍየል መንጋዎቻችሁ በኩራቱን

ሕዝቡ ከእያንዳንዱ የቤት እንስሳው በመጀመሪያ የሚወለደውን ወንድ እንዲሰጡት እግዚአብሔር ይፈልጋል