am_tn/deu/11/29.md

2.2 KiB

በረከቱን በገሪዛን ተራራ ላይ፣ መርገሙን በጌባል ተራራ ላይ ታስቀምጣላችሁ

በረከቱ እና መርገሙ አንድ ሰው በተራሮች ላይ እንደሚያስቀምጣቸው ቁሶች ተደርገው ተነግሮላቸዋል። አ.ት፡ “ከእናንተ ጥቂቱ በገሪዛን ተራራ አናት ላይ ቆማችሁ እግዚአብሔር እንዲባርካችሁ የሚያስደርገውን ቃል ታውጃላችሁ፣ ሌሎቹ በጌባል ተራራ አናት ላይ በመቆም እግዚአብሔር እንዲረግማችሁ የሚያስደርገውን ቃል ያውጃሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ገሪዛን ተራራ -- ጌባል ተራራ

እነዚህ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ የሚገኙ ተራሮች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

በሞሬ --- ከዮርዳኖስ ማዶ የሚገኙ አይደሉም?

እስራኤላውያን የሚገኙት ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምስራቅ ነው። ሙሴ እነዚህ ተራሮች የሚገኙባቸውን ስፍራዎች ለማስታወስ በጥያቄ መልክ ያቀርባል። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ተደርጎ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እንደምታውቁት ሞሬ የሚገኘው ከዮርዳኖስ ማዶ ነው” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ከዮርዳኖስ ማዶ

“ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ”

ከምዕራቡ መንገድ በስተምዕራብ

“በምስራቅ”

በጌልገላ ትይዩ

“ጌልገላ አጠገብ” ይህ ምናልባት ኢያሪኮ ከተማ አጠገብ ያለው ስፍራ ላይሆን ይችላል። ምናልባት ሙሴ ሴኬም አቅራቢያ ያለውን ስፍራ እያመለከተ ይሆናል። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

የሞሬ በሉጥ ዛፎች

እነዚህ በጌልገላ አቅራቢያ የሚገኙ የተቀደሱ ዛፎች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)