am_tn/deu/11/26.md

2.0 KiB

ተመልከቱ

“ልብ በሉ”

ዛሬ በረከትን እና መርገምን በፊታችሁ አኖራለሁ

እግዚአብሔር እንዲባርካቸው ወይም እንዲረግማቸው ይፈልጉ እንደሆነ ሕዝቡ እንዲመርጡ መፍቀዱ በረከትና መርገም ሙሴ በፊታቸው እንደሚያስቀምጣቸው ቁሶች ተደርገው ተነግሮላቸዋል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እንዲባርካችሁ ወይም እንዲረግማችሁ ዛሬ መምረጥ አለባችሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በረከቱ -- መርገሙ --

የነገር ስም የሆነው “በረከት” እና “መርገም” በግሥነት ሊተረጎሙ ይችላሉ። አ.ት፡ “… ካደረጋችሁ እግዚአብሔር ይባርካችኋል፣ … እግዚአብሔር ይረግማችኋል” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

ሌሎች አማልክትን ለመከተል እኔ ዛሬ ከማዛችሁ መንገድ ፈቀቅ ብትሉ ግን

ሙሴ ለሕዝቡ የሚነግራቸው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ እንደ እግዚአብሔር መንገድ ወይም ጎዳና ሆነው ተነግረዋል። ለእግዚአብሔር ትዕዛዝ ያለመታዘዝ ሌሎች አማልክቶችን ለመከተል በሌላ አቅጣጫ ለመመለስ ከእግዚአብሔር በአካል እንደተለዩ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ሌሎች አማልክትን ለማምለክ ዛሬ እኔ የማዛችሁን ትዕዛዝ እምቢ ብትሉ ግን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት

ይህ የሚያመለክተው ሌሎች የሕዝብ ወገኖች የሚያመልኳቸውን አማልክት ነው። እስራኤላውያን ራሱን ስለገለጠላቸውና ኃይሉን ስለተለማመዱ እግዚአብሔርን ያውቁታል።