am_tn/deu/11/24.md

1.9 KiB

የእግራችሁ ጫማ የሚረግጠውን ስፍራ ሁሉ

እዚህ ጋ “የእግራችሁ ጫማ” የሚወክለው የሰውን ሁለንተና ነው። አ.ት፡ “የምትሄዱበት ስፍራ ሁሉ” (See: Synec- doche)

ከወንዝ፣ የኤፍራጥስ ወንዝ

“ከኤፍራጥስ ወንዝ”

በፊታችሁ መቆም የሚችል ሰው አይኖርም

“በፊታችሁ መቆም” የሚለው ሐረግ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ማንም ሊያስቆማችሁ አይችልም” ወይም “ማንም ሊቃወማችሁ አይችልም”

አምላካችሁ እግዚአብሔር ማስፈራታችሁንና ማስደንገጣችሁን በምትረግጡት ምድር ሁሉ ላይ ያኖራል

እግዚአብሔር ሕዝቡ በጣም እንዲፈሩ ማድረጉ ፍርሐትና ድንጋጤን እርሱ እንደ ዕቃ በሕዝቡ ላይ እንደሚያኖራቸው በመሰለ መልኩ ተነግሯል። አ.ት፡ “አምላካችሁ እግዚአብሔር በምትሄዱበት ስፍራ ሁሉ ሕዝቡ እንዲፈሯችሁ ያደርጋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ማስፈራታችሁና ማስደንገጣችሁ

“ፍርሐት” እና “ድንጋጤ” የሚሉት ቃላት ትርጉማቸው ተመሳሳይ ሲሆን የፍርሐቱ መጠን ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “ከእናንተ የተነሣ ከባድ ፍርሐት” (See: Doublet)

በምትረግጡት ምድር ሁሉ ላይ

እዚህ ጋ “ምድሪቱ” የሚለው በምድሪቱ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች በሙሉ የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “በምትሄዱበት ስፍራ ሁሉ በሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)