am_tn/deu/11/22.md

2.0 KiB

ታደርጓቸው ዘንድ እኔ የማዛችሁን እነዚህን ትዕዛዛት ሁሉ በትጋት ብትጠብቁ

“ያዘዝኳችሁን ሁሉ ለመፈጸም ብትጠነቀቁ”

በመንገዶቹ ሁሉ ትሄዱ

አንድ ሰው እንዴት መኖርና ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር መፈለጉ እንደ እግዚአብሔር መንገድ ወይም ጎዳና ተደርጎ ተነግሯል። አንድ ሰው እግዚአብሔርን ሲታዘዝ በእግዚአብሔር መንገድ ወይም ጎዳና እንደሄደ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከእርሱ ጋር ትጣበቁ

ከእግዚአብሔር ጋር የመልካም ግንኙነት መኖርና ሙሉ በሙሉ በእርሱ ላይ መታመን አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር እንደሚጣበቅ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “በእርሱ ለመታመን” ወይም “ከእርሱ ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖር”። ተመሳሳዮቹ ቃላት በዘዳግም 10፡20 ላይ እንዴት እንደተተረጎሙ ተመልከት። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከአንተ በፊት የነበሩትን እነዚህን ሀገሮች ሁሉ፣ ሀገሮችን ታስለቅቃላችሁ

እዚህ ጋ “ሀገሮች” የሚወክሉት ቀድሞ በከነዓን ይኖሩ የነበሩትን የሕዝብ ወገኖች ነው። አ.ት፡ “ከእናንተ በፊት የነበሩትን እነዚህን የሕዝብ ወገኖች ሁሉ፣ ከሕዝብ ወገኖች ምድሪቱን ትወስዳላችሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከእናንተ ይልቅ ብዙና ኃያላን የሆኑትን

የእስራኤል ሰራዊት በከነዓን ከሚኖሩት የሕዝብ ወገኖች ይልቅ ጥቂትና ደካማ ቢሆኑም እንኳን የእስራኤል ሕዝብ ድል እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ያስችላቸዋል።