am_tn/deu/11/20.md

1.1 KiB

በቤትህ መቃኖችና በከተማህ መግቢያ በሮች ላይ ጻፋቸው

እነዚህን ቃላት በዘዳግም 6፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።

የአንተ ዕድሜና የልጆችህ ዕድሜ እንዲረዝም

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር አንተንና ልጆችህን ረጅም ዕድሜ እንድትኖሩ እንዲያደርጋችሁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ለአባቶችህ

ይህ አብርሃምን፣ ይስሐቅንና ያዕቆብን ያመለክታል።

ከምድር በላይ እስከ ሰማይ የሚደርስ ዕድሜ ይሰጣቸው ዘንድ

ሕዝቡ በምድሪቱ የሚኖሩበት ዘመን ሰማይ ከምድር በላይ ለምን ያህል ጊዜ ከመቆየቱ ጋር ተነጻጽሯል። ይህ “ለዘላለም” ብሎ የመናገር መንገድ ነው። አ.ት፡ “ለዘላለም የእነርሱ እንዲሆን ሊሰጣቸው” ወይም “በዚያ ለዘላለም እንዲኖሩ ለመፍቀድ” (See: Simile)