am_tn/deu/11/16.md

1.9 KiB

ለራሳችሁ ተጠንቀቁ

“ተጠንቀቁ” ወይም “ልብ በሉ”

ልባችሁ እንዳይታለል

እዚህ ጋ “ልብ” የሚወክለው የአንድን ሰው ምኞት ወይም አሳብ ነው። ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ምኞታችሁ እንዳያታልላችሁ” ወይም “ራሳችሁን እንዳታታልሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ትመለሱና ሌሎች አማልክትን ታመልካላችሁ

እግዚአብሔርን መተውና ሌሎች አማልክትን ማምለክ ሰው በአካሉ ከእግዚአብሔር ተለይቶ በሌላ አቅጣጫ እንደሚሄድ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ሌሎች አማልክትን ማምለክ ትጀምራላችሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የእግዚአብሔር ቁጣ በእናንተ ላይ እንዳይነድ

የእግዚአብሔር መቆጣት መንደድ እንደ ጀመረ እሳት ተደርጎ ተነግሯል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ስለዚህ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ እንዳይቆጣ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ምድር ፍሬዋን እንዳትሰጥና ዝናብን እንዳይሰጡ ሰማያትን እንዳይዘጋቸው

እግዚአብሔር ዝናብ ከሰማይ እንዳይወርድ ማድረጉ እርሱ ሰማይን እንደሚዘጋ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “በምድሪቱ ላይ ሰብል እንዳይበቅል ዝናብ ከሰማይ እንዳይዘንብ እንዳያደርግ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)