am_tn/deu/11/10.md

1.6 KiB

በእግርህ ውሃ እንዳጠጣሃት

ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች 1) “እግር” ወደ እርሻዎቹ ውሃ የመሸከምን ከባድ ሥራ የሚወክል ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ውሃ ለማጠጣት ምድከሙን” ወይም 2) ውሃ የጠጣውን እርሻ በእግሮቻቸው መገልበጥ ነበረባቸው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እጽዋት የሚበቅሉበት ስፍራ

“የአትክልት ስፍራ” ወይም “የልዩ ልዩ አትክልት ስፍራ”

ከሰማያት የዝናብን ውሃ የምትጠጣ

ምድሪቱ ብዙ ዝናብ መቀበሏና መምጠጧ ልክ ምድሪቱ ውሃውን እንደምትጠጣው ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ከሰማይ የሚወርደው ዝናብ የተትረፈረፈ ውሃ ይሰጣታል” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

የአምላክህ የእግዚአብሔር ዐይን ዘወትር በእርሷ ላይ ነው

እዚህ ጋ “ዐይኖች” የሚወክሉት ትኩረትንና ክብካቤን ነው። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር ዘወትር ይመለከታታል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ

እዚህ ጋ “መጀመሪያ” እና “መጨረሻ” የሚሉት ሁለት ጽንፎች በአንድነት ጥቅም ላይ የዋሉት ዓመቱን በሙሉ ለማለት ነው። አ.ት፡ “ሙሉውን ዓመት ባለማቋረጥ” (See: Merism)