am_tn/deu/11/06.md

1.5 KiB

የኤልያብ ልጆች ዳታንና አቤሮን

ሙሴ የሚያመለክተው ዳታንና አቤሮን በሙሴና በአሮን ላይ ያመፁበትን ያለፈውን ጊዜ ሁነት ነው። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም በይበልጥ ግልጽ መደረግ ይችላል። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

ዳታን -- አቤሮን -- ኤልያብ

እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

የሮቤል ልጅ

“የሮቤል ተወላጆች”

መሬት አፏን ከፍታ ዋጠቻቸው

እግዚአብሔር ምድሪቱ ተሰንጥቃ ሰዎች እንዲወድቁበት ማድረጉ ምድር አፍ እንዳላትና ሰዎችን የመዋጥ ችሎታ እንዳላት ተደርጎ ተነግሯል። (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

የተከተላቸው ሕይወት ያለው ሁሉ

ይህ የሚያመለክተው አገልጋዮቻቸውንና እንስሶቻቸውን ነው።

በእስራኤላውያን ሁሉ መካከል

ይህ ማለት በዳታን፣ በአቤሮን፣ በእንስሶቻቸውና በንብረታቸው ላይ ስለሆነው ነገር የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ምስክሮች ናችው።

ነገር ግን ዐይኖቻችሁ አይተዋል

እዚህ ጋ “ዐይኖች” የሚወክሉት የሰውን ሁለንተና ነው። አ.ት፡ “ነገር ግን እናንተ አይታችኋል” (See: Synecdoche)