am_tn/deu/10/08.md

1.7 KiB

ያገለግለው ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እንዲቆም

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። “እግዚአብሔር የሚያዘውን መስዋዕት እንዲያቀርብ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

በስሙ

እዚህ ጋ “ስም” ሥልጣንን ያመለክታል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔር ተወካዮች ሆነው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እንደዛሬው

“ዛሬ እንደሚያደርጉት”

የመሬት ድርሻም ሆነ ርስት

የሌዊ ነገድ ወደዚያ በደረሱ ጊዜ ከተስፋይቱ ምድር ድርሻቸውን አልተቀበሉም። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም በይበልጥ ግልጽ መደረግ ይችል ይሆናል።(See: Assumed Knowledge and Implicit Informa- tion)

እግዚአብሔር ርስቱ ነው

እግዚአብሔር ሌዊና ተወላጆቹ ከእርሱ ጋር ስለሚኖራቸው የተለየ ዝምድና ሲናገር ራሱን ሊወርሱት እንደሚችሉ አንዳች ነገር አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “እነርሱ የሚኖራቸው እግዚአብሔር ነው” ወይም “እግዚአብሔር እርሱን እንዲያገለግሉት ይፈቅድላቸዋል፣ በዚያም አገልግሎት የሚያስፈልጋቸውን ያቀርብላቸዋል”

አምላክህ እግዚአብሔር

እዚህ ጋ፣ ሙሴ እስራኤላውያንን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “የአንተ” የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)

ነገረው

“ለሌዊ ነገድ ተናገራቸው”