am_tn/deu/10/06.md

1.4 KiB

የእስራኤል ሕዝብ -- የውሃ ምንጮች ወዳሉባት ምድር

ይህ የእስራኤል ሕዝብ ወዴት እንደተጓዙ ዳራዊ መረጃ ይሰጣል። አሮንን በሞሴራ ተፈጥሮአዊ ሞት መሞቱን ደግሞ ያስታውቃል። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)

ከብኤሮት ብኔያዕቃን ወደ ሞሴራ -- ጉድጎዳ -- ዮጥባታ

እነዚህ የእስራኤል ሕዝብ በምድረ በዳ በነበሩበት ጊዜ የሄዱባቸው የተለያዩ ቦታዎች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

ብኤሮት ብኔያዕቃን

ተርጎሚው፣ “’ብኤሮት ብኔያዕቃን’ የሚለው ስም ‘የያዕቃን ሰዎች የውሃ ጉድጓድ’ ማለት ነው” የሚል የግርጌ ማስታወሻ መጨመር ይኖርባቸው ይሆናል።

በዚያ ተቀበረ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እርሱን የቀበሩት በዚያ ነው” ወይም “እስራኤላውያን በዚያ ቀበሩት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

አልዓዛር

ይህ የአሮን ልጅ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)