am_tn/deu/09/25.md

1.3 KiB

በእግዚአብሔር ፊት በግምባር መደፋት

“በመሬት ላይ በግምባሬ ተደፋሁ”። ይህንን በዘዳግም 9፡18 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

አርባ ቀንና አርባ ሌሊት

“40 ቀንና 40 ሌሊት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)

የተቤዠኸውን

እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ገንዘብ በመክፈል ከባርነት ነጻ እንዳደረጋቸው በሚመስል መልኩ ሙሴ ይናገራል። አ.ት፡ “አድነሃቸዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በታላቅነትህ

“ታላቅነት” የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ታላቅ ኃይል የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “በታላቅ ኃይልህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በብርቱ እጅ

እዚህ ጋ “ብርቱ እጅ” የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ኃይል ነው። ተመሳሳዮቹን ቃላት በዘዳግም 4፡34 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “በብርቱ ኃይልህ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)