am_tn/deu/09/22.md

1.4 KiB

ተቤራ -- ማሳህ -- ቂብሮት ሐታአዋ

እነዚህ የእስራኤል ሕዝብ በምድረ በዳ በነበሩበት ጊዜ የሄዱባቸው የተለያዩ ቦታዎች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

ውጡ

እግዚአብሔር ሊሰጣቸው የነገራቸው ምድር በኮረብታዎቹ ላይ ያለ ሲሆን እነርሱ የነበሩት ቆላው ላይ ነው፣ ስለዚህ ያገኙት ዘንድ ወደ ኮረብታዎቹ መውጣት ነበረባቸው።

በትዕዛዙ ላይ አመፃችሁ

“ትዕዛዝ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ራሱን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ላይ አመፃችሁ፤ ትዕዛዙንም አልጠበቃችሁም” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ድምፁን መስማት

እዚህ ጋ “ድምፁን” ማለት እግዚአብሔር ተናግሮችት የነበረውን ነው። አ.ት፡ “የተናገረውን ታዘዙት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ካወቅዃችሁ ጊዜ ጀምሮ

“ልመራችሁ ከጀመርኩበት ጊዜ አንሥቶ”። አንዳንድ ትርጉሞች “ካወቃችሁ ጊዜ ጀምሮ”፣ ለመጀመሪያ ጊዜ እግዚአብሔር እነርሱን ያወቀበት ቀን በሚል ይነበባሉ