am_tn/deu/08/15.md

1.7 KiB

በመጨረሻ -- የመራህን

ሙሴ ለእስራኤላውያን ስለ እግዚአብሔር የሚያውቁትን ማስታወስ ቀጥሏል (ዘዳግም 8፡14)። (ለይቶ ማሳወቅ ማሳወቅን ወይም ማስታወስን ሲቃረን የሚለውን ተመልከት)

የመራህ -- ያመጣህ -- መገበህ

“የመራህ እግዚአብሔር … ያመጣህ እግዚአብሔር … እግዚአብሔር መገበህ”

ተናዳፊ እባብ

“መርዘኛ እባብ”

የተጠማ ምድር

ይህ ሐረግ ልክ ሰው ውሃ በሚፈልግበት ጊዜ እንደሚጠማ ምድሪቱ መጠማቷን ይገልጻል። አ.ት፡ “ደረቅ ምድር” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

መልካም ሊያደርግልህ

“ሊረዳህ” ወይም “ለአንተ መልካም ስለነበረ”

ሆኖም በልብህ -- ትል ይሆናል

ይህ ምናልባት ሰዎች ልባቸው “በሚታበይበት” እና “እግዚአብሔርን በሚረሱበት” ጊዜ የሚያደርጉት ሦስተኛው ነገር ነው። (ዘዳግም 8፡14)። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ኃይሌና የእጄ ብርታት ይህንን ሁሉ ሀብት አስገኘልኝ

እዚህ ጋ “እጅ” የሚያመለክተው የአንድን ሰው ኃይል ወይም ችሎታ ነው። አ.ት፡ “እኔ በጣም ብርቱና ኃይለኛ ስለሆንኩኝ ይህንን ሀብት አግኝቻለሁ” ወይም “እነዚህን ነገሮች ሁሉ በራሴ ኃይልና ችሎታ አግኝቻለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)