am_tn/deu/08/09.md

1.2 KiB

የምትበላውን እንጀራ የማታጣባት ምድር

ይህ ምጸታዊ አነጋገር በአዎንታዊነት ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የተትረፈረፈ ምግብ የምታገኝበትን ምድር” (ምጸት የሚለውን ተመልከት)

ምንም ነገር የማታጣበትን ሀገር

ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የምትፈልገውን ሁሉ የምታገኝበት” (ድርብ አሉታዊ የሚለውን ተመልከት)

ድንጋዮቹ ብረት የሆኑበት

ድንጋዮቹ በብረት ማዕድን የተሞሉ ናቸው። የብረት ማዕድን ሰይፍና ማረሻ ለመሥራት የሚያገለግል ጠንካራ ብረት ነው።

መዳብ ትቆፍራለህ

“የመዳብ ማዕድን ታወጣለህ”። መዳብ የቤት ውስጥ መገልገያዎችን ለመሥራት የሚያገለግል ለስለስ ያለ ብረት ነው።

ትበላለህ፣ ትጠግባለህም

“እስክትጠግብ ድረስ የምትበላው በቂ ምግብ ይኖርሃል”

ትባርካለህ

“ታመሰግናለህ” ወይም “ምስጋናን ታቀርባለህ”