am_tn/deu/08/03.md

1.3 KiB

ትሁት አደረገህ

“እግዚአብሔር ምን ያህል ደካማና ኃጢአተኛ መሆንህን አሳየህ”። በዘዳግም 8፡2 ላይ “ትሁት ሊያደርግህ” የሚለው ቃል እንዴት እንደተተረጎመ ተመልከት።

መናን መገበህ

“እንድትበላው መናን ሰጠህ”

ሰዎች በሕይወት የሚኖሩት በእንጀራ ብቻ አይደለም

እዚህ ጋ “እንጀራ” የሚወክለው ሁሉንም የምግብ ዓይነት ነው። አ.ት፡ “ሰዎች በሕይወት ለመኖር እንዲችሉ የሚፈልጉት ምግብ ብቻ አይደለም” (See: Synecdoche)

ሰዎች በሕይወት የሚኖሩት ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ ነው

እዚህ ጋ “የእግዚአብሔር አፍ” በፈሊጣዊ አነጋገር እግዚአብሔር የሚናገረው ቃል ማለት ነው። አ.ት፡ “ሰዎች በሕይወት መኖር እንዲችሉ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ መታዘዝ አለባቸው” ወይም “ሰዎች በሕይወት መኖር እንዲችሉ እግዚአብሔር የሚነግራቸውን መፈጸም አለባቸው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)