am_tn/deu/07/25.md

2.0 KiB

ታቃጥላለህ

ይህ ትዕዛዝ ነው።

አማልክቶቻቸውን

“የሌሎች ሕዝቦችን አማልክት”

አትቅና -- በእርሱ አትጠመድ

እነዚህ ቃላት አማልክቶቹን እንዲያቃጥሉ በተሰጣቸው መመሪያ ላይ ተጨማሪዎች ናቸው

በእርሱ ትጠመዳለህ

በጣዖታቱ ላይ ያለውን ወርቅ ወይም ብር መውሰድ እንኳን ሕዝቡ እንዲያመልኳቸው ሊያደርጋቸው ይችላል። ይህንን በማድረጋቸው በወጥመድ እንደተያዘ እንስሳ ይሆናሉ። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ወጥመድ ይሆንባችኋል” (See: (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት))

ይህ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አስጸያፊ ነው

እነዚህ ቃላት ሕዝቡ ጣዖታቱን እንዲያቃጥሉ እግዚአብሔር ለምን እንደፈለገ ይነግሩናል። “አምላካችሁ እግዚአብሔር በጣም ስለሚጠላው ይህንን አድርጉ”

ፈጽመህ ትጠላዋለህ፣ ትጸየፈዋለህም

“መጥላት” እና “መጸየፍ” የሚሉት ቃላት መሠረታዊ ትርጉማቸው አንድ ሆኖ ሳለ ለጥላቻው ጥልቅነት አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “ፈጽመህ ትጠላዋለህ” (See: Doublet)

እርሱ ለጥፋት የተለየ ነው

እግዚአብሔር አንድን ነገር መርገሙና ሊያጠፋው መማሉ ነገሩን ከየትኛውም ነገር ለይቶ እንደሚያስቀምጠው ሆኖ ተነግሯል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እርሱን እግዚአብሔር ለጥፋት ለይቶ አስቀምጦታል” (See: (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊድምፅ የሚለውን ተመልከት))