am_tn/deu/07/17.md

1.7 KiB

በልብህ ---- ብትል -- አትፍራ

ሀገራቱ ከእነርሱ ይልቅ ብርቱዎች እንደሆኑ ቢያስተውሉም እንኳን ሕዝቡ መፍራት የለባቸውም። አ.ት፡ “ምንም እንኳን በልብህ -- ብትናገር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

በልብህ ብትናገር

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ብታስብ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

እንዴት ላስወጣቸው እችላለሁ?

ሕዝቡ ሌሎች አገራትን ስለ ፈሩበት ስሜት አጽንዖት ለመስጠት ሙሴ በጥያቄ መልክ ይጠቀማል። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል።አ.ት፡ “ላሸንፋቸው አልችልም” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

አስታውስ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ማስታወስ አለብህ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ዐይኖችህ ዐይተዋል

እዚህ ጋ “ዕይኖችህ” የሚወክለው የሰውን ሁለንተና ነው። አ.ት፡ “ያየኸው” (See: Synecdoche)

ጽኑውን እጅ፣ የተዘረጋችውንም ክንድ

እዚህ ጋ “ጽኑ እጅ” እና “የተዘረጋች ክንድ” የእግዚአብሔርን ኃይል የሚገልጹ ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው። ይህንን በዘዳግም 4፡34 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እና በጽኑ ኃይሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)