am_tn/deu/07/14.md

1.6 KiB

ከሌሎች ሕዝቦች የበለጠ ትባረካለህ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሌሎች ሕዝቦችን ከምባርክበት በበለጠ እባርክሃለሁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በመካከልህ ወይም በከብቶችህ መካከል የማይወልድ ወንድ ወይም መካን ሴት አይኖርም

ሙሴ ሁሉም ልጆች ሊኖሯቸው እንደሚችሉ አጽንዖት ለመስጠት አሉታዊ መግለጫዎችን ይጠቀማል። ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እናንተ ሁላችሁም ልጆች ይኖሯችኋል፣ ከብቶቻችሁም ይበዛሉ” (ምጸት የሚለውን ተመልከት)

በመካከልህ -- ከብቶችህ

“አንተ” እና “የአንተ” የሚሉት ቃላት ብዙ ቁጥር ናቸው። (See: Forms of You)

በሽታን ሁሉ ከአንተ አርቃለሁ

“እንደማትታመም እርግጠኛ ሁን” ወይም “ፍጹም ጤና እንድትሆን እጠብቅሃለሁ”

በአንተ ላይ -- ክፉ በሽታዎችን ሁሉ፣ ነገር ግን በሚጠሉህ ሁሉ ላይ ያመጣቸዋል

ሙሴ በሽታን እግዚአብሔር በሰዎች ጫንቃ ላይ እንደሚጭነው ከባድ ቁስ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “እርሱ በየትኛውም ክፉ በሽታ እንድትታመም አያደርግህም … ነገር ግን ጠላቶችህ በእነርሱ እንዲታመሙ ያደርጋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)