am_tn/deu/06/13.md

2.0 KiB

አምላክህን እግዚአብሔርን ታከብራለህ፤ እርሱንም ታመልካለህ፣ በእርሱም ስም ትምላለህ

“ማክበር የሚኖርብህ አምላክህን እግዚአብሔርን እንጂ ሌላውን አይደለም፤ ማምለክ ያለብህ እርሱን ብቻ ነው፣ መማል የሚኖርብህም በእርሱ ስምና በእርሱ ስም ብቻ ነው”። እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ሌሎች አማልክቶችን እንዳያመልኩ ወይም እንዳያገለግሉ ስለመናገሩ ምናልባት የአንተ ቋንቋ አጽንዖት የሚሰጥበት ሌላ መንገድ ይኖር ይሆናል።

በስሙ ትምላለህ

በእግዚአብሔር ስም መማል ማለት እግዚአብሔርን የመሓላው መሠረት ወይም ኃይል ማድረግ ማለት ነው። “በስሙ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ራሱን ነው። አ.ት፡ “ትምላለህ፣ እግዚአብሔር እንዲያጸናውም ትጠይቃለህ” ወይም “በምትምልበት ጊዜ ስሙን ትጠራለህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በመካከልህ

“በመካከልህ የሚኖር”

የአምላክህ የእግዚአብሔር ቁጣ በአንተ ላይ ይነዳል

ሙሴ የእግዚአብሔርን ቁጣ አንድን ነገር ለማቃጠል እሳት ከሚለኩስ ሰው ጋር ያነጻጽረዋል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። ቁጣን መለኮስ በጣም የመቆጣት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር ቁጣውን ያነዳል” ወይም “አምላክህ እግዚአብሔር በጣም ይቆጣል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከ -- ያጠፋሃል

“ምንህም እስከማይተርፍ ድረስ ያጠፋሃል”