am_tn/deu/06/04.md

782 B

አምላካችን እግዚአብሔር አንድ ነው

“አምላካችን እግዚአብሔር አንድና ብቸኛ አምላክ ነው”

በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና በሙሉ ኃይልህ

እዚህ ጋ “ልብ” እና “ነፍስ” የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። እነዚህ ሦስቱ ሐረጎች በአንድነት ጥቅም ላይ የዋሉት “በፍጹም” ወይም “በቅንነት” ለማለት ነው። በዘዳግም 4፡29 ላይ “በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ” የሚለውን እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Doublet የሚለውን ተመልከት)