am_tn/deu/02/24.md

2.5 KiB

አሁን ተነሡ

ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር ለሙሴ እየነገረው ነው። “አሁን ተነሡ” ወይም “አሁን ሂዱ”

መንገዳችሁን ሂዱ

“ጉዞአችሁን ቀጥሉ”

የአርኖን ሸለቆ

ይህ የአርኖን ወንዝ ሸለቆ ስም ነው። እርሱ በሞዓብና በአሞራውያን መካከል ድንበር ያበጃል። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

በእጃችሁ ሰጥቻችኋለሁ

“በእጃችሁ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ትርጉም “በቁጥጥራችሁ ወይም በኃይላችሁ ሥር” ማለት ነው። አ.ት፡ “እንድታሸንፉ ኃይልን ሰጥቻችኋለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እጃችሁ - ለመውረስ ጀምሩ - ተዋጉ - ማስፈራታችሁ - ዝናችሁ - በእናንተ ምክንያት

ሙሴ ለእስራኤላውያን አንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ በመሆኑም “አንተ” እና “የእናንተ” እንዲሁም ትዕዛዝ የሆኑት “ለመውረስ ጀምሩ” እና “ተዋጉ” ሁሉም አገባቦች ነጠላ ቁጥሮች ናቸው። (See: Forms of You)

ሴዎን

ይህ የአንድ ንጉሥ ስም ነው። ይህንን በዘዳግም 1፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

ሐሴቦን

ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። ይህንን በዘዳግም 1፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

ከእርሱ ጋር ተዋጋ

“ከእርሱና ከሰራዊቱ ጋር ተዋጋ”

አስፈሩ፣ አስደንግጡም

“ፍርሐት” እና “ድንጋጤ” የሚሉት ቃላት መሠረታዊ ትርጉማቸው አንድ ቢሆንም ፍርሐቱ ታላቅ መሆኑን አጽንዖት ይሰጣል። አ.ት፡ “ከባድ ፍርሐት ጣሉባቸው” (See: Doublet)

ከሰማይ በታች ያለ ሕዝብ ሁሉ

ይህ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “በየአገሩ ያሉ ሕዝቦች” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ይንቀጥቀጡና ይጨነቁ

ይህ ሕዝቡ በጭንቀት እንደሚንቀጠቀጡ አጽንዖት ይሰጣል። (See: Hendiadys)