am_tn/deu/01/07.md

1.3 KiB

ተመልሳችሁ ጉዞአችሁን ቀጥሉ

“ተመልሳችሁ” የሚለው ቃል አንድን ተግባር ለመጀመር ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “እንደገና ጉዞአችሁን ቀጥሉ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ኮረብታማ አገር -- ኤፍራጥስ

እግዚአብሔ ለእስራኤላውያን ለመስጠት ቃል በገባላቸው ምድር አካባቢዎቹን እያብራራላቸው ነው።

ኮረብታማ አገር

ይህ አሞራውያን ይኖሩ ከነበሩበት አቅራቢያ የሚገኝ ኮረብታማ አካባቢ ነው።

ቆላ

ዝቅና ለጥ ያለ የምድር አካባቢ

ተመልከት

“ለምናገረው ነገር ትኩረት ስጡ”

ምድሪቱን በፊታችሁ አስቀምጫለሁ

“አሁን ይህችን ምድር ሰጥቻችኋለሁ”

እግዚአብሔር የማለላችሁን ያንን

እግዚአብሔር ራሱን እንደ ሌላ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “እኔ እግዚአብሔር ምያለሁ” (ተውላጠ ስም የሚለውን ተመልከት)

አባቶች

“አባቶች” የሚለው ቃል አያት፣ ቅድም አያቶችን ሁሉ የሚወክል ነው። አ.ት፡ “አያት፣ ቅድም አያቶች” (See: Synecdoche)