am_tn/dan/11/40.md

1.6 KiB

በፍፃሜ ዘመንም

“የመጨረሻ ቀናት”ወይም “የዓለም መጨረሻ”

የደቡቡ ንጉሥ …የሰሜኑ ንጉሥ

እነዚህ ሐረጎች ነገሥታቱንና ሠራዊታቸውን የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ “የደቡቡ ንጉሥና ሠራዊቱ ”….“የሰሜኑ ንጉሥና ሠራዊቱ”

እንደ አውሎ ነፋስ ይመጣበታል

ከባድ በሆነ ውጊያ ጠላትን ለማጥቃት ልክ አውሎ ነፋስ እንደተነሳ ተደርጎ ነው የሚነገረው፡፡“እንደ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ጥቃት ይሰነዝርበታል”ወይም “በብርቱ ይዋጋል”

ይጎርፍማል

አንድ ሠራዊት አገሩን ሲወርር ጎርፍ እንደተከሰተ ዓይነት ተደርጎ ነው የሚነገረው፡፡

ያልፍማል

ሠራዊቱን የሚያቆም ኃይል አይኖርም፡፡“ማንም ሊያስቆመው በማይችል መልኩ በምድሪቱ ውስጥ ያልፋል፡፡”

መልካሚቱ ምድር

ይሄ የሚያመለክተው የእሥራኤልን ምድር ነው፡፡

ይወድቃል

እዚህ ላይ መውደቅ የሚለው ቃል የሚያመለክተው የመሞትን ድርጊት ነው፡፡“ይሞታል”

ነገር ግን እነዚህ ከእጁ ይድናሉ

እዚህ ላይ“እጅ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኃይልን ነው፡፡“ነገር ግን እነዚህ ከእርሱ ኃያል ጥቃት ያመልጣሉ”ወይም “ነገር ግን እነዚህን አገሮች ለማጥፋት ይሳነዋል”