am_tn/dan/11/36.md

2.6 KiB

X

“ንጉሡ የወደደውን ሁሉ ያደርጋል”

ንጉሡ

ይሄ የሚያመለክተው የሰሜኑን ንጉሥ ነው፡፡

ራሱንም ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ራሱን ታላቅ ያደርጋል

“ራሱንም ከፍ ከፍ ያደርጋል”የሚለውና ”ራሱን ታላቅ ያደርጋል” የሚለው ቃልተመሳሳይ ዓይነት ትርጉም ያላቸው ሲሆን ንጉሱ እጅግ የሚኮራ እንደሆነ ይጠቁማሉ፡፡

ራሱን ከፍ ከፍ ያደርጋል

እዚህ ላይ ይሄ የሚያመለክተው እጅግ እየኮራ መሆኑን ነው፡፡

ራሱን ታላቅ አደረገ

እዚህ ላይ ይሄ የሚያመለክተው እጅግ አስፈላጊ ሰውና ኃያል ሰው ለመሆን የማስመሰሉን ነገር፡፡

የአማልዕክት አምላክ

ይሄ የሚያመለክተው እውነተኛ ሆነውን አንዱን አምላክ ነው፡፡“ታላቅ የሆነውን እግዚአሔር” ወይም“እርሱ ብቻ እውነት የሆነ አምላክ”

አስገራሚ ነገሮች

“አሰቃቂ ነገሮች”ወይም“አስደንጋጭ ነገሮች”

ቁጣውም አስኪፈፀም ድረስ

ይህ ሐረግ መጋዘኑ ፈፅሞ እስኪሞላ ድረስ ቁጣውን እንደሚያከማችና በኋላም ወደ ተግባር እንደሚገባ ዓይነት አድርጎ ነው የሚገልፀው፡፡“የእግዚአብሔር ቁጣ የመጨረሻ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ”ወይም“እርምጃ ለመውሰድ ይችል ዘንድ የእግዚአብሔር ቁጣ ጫፍ እስኪደርስ ድረስ”

በሴቶች ዘንድ የሚወደድ አማልዕክት

ይሄ የአህዛብ ጣኦት የሆነውንና ታሚዝ በሚል ሥያሜ የሚታወቀውን ጣኦት የሚያመለክት ይመስላል፡፡

የአምባዎች አምላክ

ምናልባትም ይሄ ንጉሥ ይሄ የሐሰት አምላክ የሌሎች ሰዎችን ምሽጎች እያጠቃ የእርሱን ይዞታ ግን በሰላም እንዲጠበቅ የሚያደርግለት መሆኑን አምኖ ሊሆን ይችላል፡፡“ምሸጎችን የሚጠብቅ የጣዖት አምላክ”

በእነዚህ ፋንታ

“እነዚህ”የሚለው ቃል በትንቢተ ዳንኤል 11፡37 ላይ የተጠቀሱትን ጣዖታት የሚያመለክት ነው፡፡

ምድርንም በዋጋ ይከፍላል

ለዚህ ትርጉም ሊሆኑ የሚችሉት 1/“ምድሪቱን በሥጦታ መልክ ለተከታዮቹ ይሰጣል”ወይም 2/“ለተከታዮቹ መሬቱን ይሸጣል፡፡”