am_tn/dan/11/20.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

መልአኩ ለዳንኤል መናገሩን ይቀጥላል፡፡

በእርሱም ሥፍራ ሌላ ሰው ይነሣል

በንጉሱ ቦታ ላይ ሌላ ሰው ይነሣል ማለት ቀድሞ በነበረው ንጉሥ ቦታ ላይ ሌላ ሰው ይቀመጣል ማለት ነው፡፡“በዚያ ንጉሥ ምትክ ሌላ ሰው የሰሜን ንጉሥ ይሆናል፡፡”

እርሱ ይሰበራል

እዚህ ላይ “እርሱ”የሚለወው ቃል የሚያመለክተው አዲሱን ንጉሥ ነው፡፡መሰበር የሚለው ቃል የሚመለክተው መሞትን ነው፡፡“የአዲሱ ንጉሥ ሕይወት ያልፋል፡፡”

በቁጣ ሣይሆን

ለዚህ ሃሣብ ትርጉም ሊሆኑ የሚችሉት 1/ማንም ሰው በንጉሡ ላይ አልተበሳጨም 2/የንጉሱ የሞቱ ሁኔታና ምክኒያት በምሥጢር መያዛቸው፡፡

ሕዝቡ የመንግሥትነትን ሥፍራ ሊሰጠው የማይፈልገው የተጠላ ሰው

የንጉሥ ዘር ባለመሆኑ ምክኒያት ሕዝቡ እርሱን እንደ ንጉሥ ለመቀበል ፈቃደኛ አይሆንም፡፡“የማይቀበሉትና ንጉሥ እንዳይሆን የሚፈልጉት ሰው”

የሚጎርፍም ሠራዊት ከፊቱ ይወሰዳል

ይወሰዳል የሚለው ቃል የሚወክለው ይጠፋል የሚለውን ቃል ነው፡፡“ጎርፍ በሚጓዝበት ነመንገድ ሁሉ ያለውን ነገር እያጠፋ እንደሚሄድ ሁሉ እንደዚሁ እርሱም ታላቅ ሠራዊትን ያጠፋል፡፡”

እርሱና የቃል ኪዳኑ አለቃ ይሰበራሉ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሠራዊቱንና የቃል ኪዳኑን አለቃ ያጠፋል”

የቃል ኪዳኑ አለቃ

የካህናቱ መሪ፡፡“ይሄ ሐረግ እግዚአብሔር በቃል ኪዳኑ ውስጥ እጅግ ከፍተኛ የሆነውን ኃይማኖታዊ ሥልጣን የያዘውን ሰው ማለትም ሊቀ ካህንንየሚያመለክት ነው፡፡”