am_tn/dan/11/15.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

መልአኩ ለዳንኤል መናገሩን ይቀጥላል፡፡

የሰሜኑም ንጉሥ ይመጣል

“የሰሜኑ ንጉሥ”የሚለው ቃል የእርሱንም ሠራዊት ያካትታል፡፡“የሰሜኑ ንጉሥ ሠራዊት ይመጣል፡፡”

ጉብታዎችን ይወስድ ዘንድ አፈርን ይደለድላል

ይሄ የሚያመለክተው ሠራዊቱ በእነርሱ ላይ ጥቃት ለማድረስ ይችል ዘንድ የከተማዋ ከፍታ ቦታ ላይ ለመድረስ አፈር የመደልደላቸውን ሁኔታ ነው፡፡ወታደሮችን ባሪያዎች በቅርጫት ውስጥ አፈር በማስቀመጥ ወደ ከፍታ ቦታ ላይ ከወሰዱት በኋላ ጉብታ እንዲፈጥርላቸው ይከምሩታል፡፡

ምሽግ መሥራት

አንድን ከተማ ከጠላት ለመከላከል የሚገነባ ቅጥር ወይም በወታደሮች አማካይነት የጠላት ወታደሮችን ለመከላከል የሚገነባ ምሽግ፡፡

በፊቱም የሚቆም የለም

እዚህ ላይ የሚቆም የሚለው ቃል የሚያመለክተው የመዋጋት ብቃቱን ነው፡፡“ከእነርሱ ጋር እየተዋጉ መቀጠል ያዳግታቸዋል፡፡”

በእርሱም ላይ የሚመጣው ግን እንደ ፈቃዱ ያደርጋል

“ወራሪው ንጉሥ በዚያኛው ንጉሥ ላይ የፈለገውን ነገር ሊያደርግ ይችላል፡፡”

ይቆማል

እዚህ ላይ መቆም የሚያመለክተው መግዛትን ነው፡፡“ንጉሱ መግዛት ይጀምራል”

መልካሚቱ ምድር

ይሄ የሚያመለክተው የእሥራኤልን ምድር ነው፡፡ይሄንን በትንቢተ ዳንኤል 8፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡

በእጁም ውስጥ ጥፋት ይሆናል

እዚህ ላይ “ጥፋት”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የማውደምን ኃይል ነው፡፡የማጥፋት ኃይል የሚለው አባባል አንድ ሰው በእጁ ሊይዘው እንደሚችል ዓይነት ቁስ ተደርጎ ነው የተገለፀው፡፡“ማንኛውንም ነገር የማጥፋት ኃይል አለው፡፡”