am_tn/dan/11/11.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

መልአኩ ለዳንኤል መናገሩን ይቀጥላል፡፡

ብዙ ሕዝብንም ለሠልፍ ያቆማል

“ታላቅ ሠራዊትን ይሰበስባል”

ሠራዊቱም አልፎ በእጁ ይሰጣል

እዚህ ላይ“እጅ”የሚለው ቃል የሚወክለው የሰሜኑ ንጉሥ ተቆጣጣሪ መሆኑን ነው፡፡“ንጉሡ ሠራዊቱን ለደቡቡ ንጉሥ አሣልፎ ይሰጣል፡፡”

ሠራዊቱ ይጋዛል

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችል ይሆናል፡፡“የደቡቡ ንጉሥ የሰሜኑን ሠራዊት ይማርካል”

ይታበያል

ይታበያል የሚለው ቃል የሚያመልከተው እጅግ ኩራተኛ መሆኑን ነው፡፡“እጅግ ይኮራል”

አዕላፋትንም እንዲወድቁ ደርጋል

እዚህ ላይ መውደቅ የሚለው ቃል የሚያመለክተው በጦርነት ውስጥ መሞትን ነው፡፡“ሠራዊቱ ከጠላቶቹ መካከል ብዙ ሺዎችን እንዲገድሉ ያደርጋል፡፡” ወይም “በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ጠላቶቹን የሚገድል ይሆናል፡፡”

አዕላፍ

“ብዙ ሺዎች”