am_tn/dan/11/01.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

በትንቢተ ዳኤል ከምዕራፍ11፡1 እስከ ምዕራፍ 12፡4 ድረስ ባለው ክፍል ውስጥ በምዕራፍ 10 ላይ ለዳንአል የሚናገረው በእውነት መፅሐፍ ላይ የተፃፈውን ነው፡፡ይሄ በትንቢተ ዳንኤል 10፡21 ላይ እፈፅመዋለሁ ብሎ እንደተናገረው ነው፡፡

በዳርዮስ በመጀመሪያ ዓመት

ዳርዮስ የሜዶን ንጉሥ ነበረ፡፡“የመጀመሪያው ዓመት”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ንጉሥ የሆነበትን የመጀመሪያውን ዓመት ነው፡፡“በመጀመሪያው በዳርዮስ የአገዛዝ ዘመን”

ሦስት ነገሥታት በፋርስ ይነሣሉ

“ሦስት ነገሥታት በፋርስ ላይ ይነግሳሉ”

አራተኛውም ከሁሉ ይልቅ እጅግ ባለጠጋ ይሆናል

“ከእነርሱ በኋላ ከሦስቱ ይልቅ ብዙ ገንዘብ ያለው አራተኛ ንጉሥ ሥልጣኑን ይይዛል”

ኃይል

ለዚህ ቃል ትርጉም ሊሆኑ የሚችሉት 1/ሥልጣን2/የወታደር ኃይል

ሁሉን ያስነሳል

“ሁሉንም ሰዎች ለመዋጋት ፈቃደኞች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል”