am_tn/dan/10/16.md

1.3 KiB

የሰው ልጅ የሚመስል

ይሄ ምናልባት ከዳንኤል ጋር የተነጋገረውን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል፡፡ሆኖም አንዳንድ ቅጂዎች ከሌላ ሰው ጋር እንደተነጋገረ አድርገው ነው የተረጎሙት፡፡“ይሄኛው፤የሰው ልጅ የሚመስለው”

የሰው ልጅ የሚመስለው

ይሄ አገላለፅ የሚያመለክተው በአጠቃላይ የሰው ልጆችን ነው፡፡“እንደ ሰው ልጅ”

ጭንቀት

ብርቱ የሆኑ ስሜታዊ ሕመሞች

ይህ የጌታዬ ባሪያ ከጌታዬ ጋር ይናገር ዘንድ እንዴት ይችላል?

ዳንኤል ይህንን ጥያቄ በሚጠይቅበት ጊዜ እኔ ከመልአክ ጋር በእኩል ደረጃ መነጋገር የምችል ሰው ስላልሆንኩ ከመልአክ ጋር መነጋገር አልችልም ማለቱ ነው፡፡እነዚህ ዓረፍተ ነገሮች ሊጣመሩ ይችላሉ፡፡“የአንተ ባሪያ ስለሆንኩ መልስ ልሰጥህ አልችልም”

እስትንፋስም አልቀረልኝም

ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያመለክተው መተንፈስን ነው፡፡“መተንፈስ አልቻልኩም” ወይም “ለመተንፈስ ከባድ ነው፡፡”