am_tn/dan/10/07.md

1.3 KiB

እኔም ብቻዬን ቀርቼ ራዕዩን ተመለከትኩ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ማንም አጠገቤ አልነበረም፡፡እናም አየሁ”

ደም ግባቴም ወደ ማሸብሸብ ተለወጠብኝ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“መልካም የነበረው ገፅታዬ ወደ አስከፊ ገፅታ ተለወጠ”

ደም ግባቴ

ይሄ የሚያመለክተው ጤነኛ የሆነን ሰው ገፅታ ነው፡፡“ጤነኛ ገፅታ ያለው ፊቴ”

የፈራረሰ ገፅታ

ጤነኛ ያልሆነና የገረጣ ፊት ከሚፈርስ ሕንፃ ጋር ተመሳስሎ ቀርቧል፡፡“የገረጣ”

የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ

ይሄ አንድ ሰው በራዕዩ ውስጥ ያነጋግረው እንደነበረ የሚያሣይ ነው፡፡ይሄ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“የሆነ ሰው የሚናገረውን ንግግር ሰማሁ”

ደንግጬ በምድር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ

ለዚህ ትርጉም ሊሆኑ የሚችሉት 1/ዳንኤል ካየው ነገር የተነሳ እጅግ በመፍራቱ በምድር ላይ ተደፍቶ ራሱን ሳተ 2/ዳንኤል ራሱን ከሳተ በኋላ በምድር ላይ ተደፋ፡፡