am_tn/dan/10/04.md

2.0 KiB

ከመጀመሪያውም ወር በሃያ አራተኛው ቀን

ይሄ የዕብራውያን የመጀመሪያ ወር ነው፡፡በምዕራባውያን የቀን አቆጣጠር መሠረት ሃያ አራተኛው ቀን የሚውለው በመጋቢት ወር አጋማሽ አካባቢ ነው፡፡

ወገቡን የታጠቀ

“ቀበቶ አድርጎ ነበር”

አፌዝ

አፌዝ የቦታ ሥፍራ ነው፡፡ያለበት ትክክለኛ ሥፍራ አልተገለፀም፡፡

ሰውነቱ እንደ ቶፓዝ ነበረ

ሰውነቱ ከቶፓዝ የተሰራ ይመስልበሰማያዊና በቢጫ ብርሃን ያብረቀርቅ ነበር፡፡“ሰውነቱ እንደ ቶፓዝ አብረቀረቀ”

ቶፓዝ

ሰማያዊ ወይም ቢጫ የከበረ ድንጋይ ሲሆኑ ቤሪል፤ፔሪዶትና ክራሶላይት በመባልም ይታወቃሉ፡፡

ፊቱም እንደ መብረቅ አምስያ ነበረ

ፊቱ ልክ መብረቅ አበራ፡፡“ልክ እንደመብረቅ ብርሃን ፊቱ በብርሃን ደመቀ”

ዓይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና

የሚንበለበሉ ችቦዎች ይመስልዓይኖቹ እጅግ ብሩህ ነበሩ፡፡“ዓይኖቹ ብሩህ ከመሆናቸው የተነሣ ችቦዎች ዓይኖቹ ውስጥ የሚንበለበሉ ይመስል ነበር፡፡”

ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ

ከተወለወለ ነሐስ የተሰሩ ይመስል ክንዶቹና እግሮቹ ያብረቀርቁ ነበር፡፡“ከንዶቹና እግሮቹ የተወለወለ ነሐስ ይመስል ከውስጣቸው የሚፈልቀው ብርሃን አካባቢውን ሁሉ ያዳርሳል፡፡”

የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ

ድምፁ ከሙጉላቱ የተነሣ ብዙ ሰዎች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚነጋገሩ ይመስላል፡፡ ድምፁ ከመጉላቱ የተነሣ ብዙ ሰዎች በጋራ ጮኸው የሚጣሩ ነው የሚመስለው፡፡