am_tn/dan/09/26.md

1.4 KiB

ስድሳ ሁለት ሱባዔዎች

ይሄ እሥራኤላውያን የሚቆጥሩበት የተለመደ የአቆጣጠር ዓይነት አይደለም፡፡“ስድሣ ሁለት ጊዜ ሰባት”

መሢሁም ይገደላል፤በእርሱም ዘንድ ምንም አይኖርም

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሰዎች መሢሁን ያጠፉታል፤ምንም ነገር አይቀርለትም”

የተቀባው

መቀባት የሚለው ቃል አንድ ሰው መመረጡን የሚያሣይ ተምሣሌታዊ ድርጊት ነው፡፡“እግዚአብሔር የሚቀባው ሰው” ወይም “እግዚአብሔር የሚመርጠው ሰው ”

የሚመጣው አለቃ

ይሄ ባዕድ የሆነ ገዢ እንጂ “የተቀባው ገዢ”አይደለም፡፡“የሚመጣው ባዕድ ገዢ”ወይም “የሚመጣው ኃይለኛ ገዢ”

ፍፃሜውም በጎርፍ ይሆናል

ሠራዊቱ ከተማዋንና ቅዱስ ሥፍራውን ጎርፍ ነገሮችን እንደሚያጠፋ እንዲሁ ያጠፉታል፡፡

ጥፋትም ተቆጥሯል

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር በከተማዋና በመቅደሱ ላይ ጥፋትን አዝዟል”ወይም “እግዚአብሔር ሠራዊቱ ሁሉንም ነገር እንዲያጠፋ አዝዞታል”