am_tn/dan/09/24.md

2.6 KiB

ሰባ ሱባዔዎች...ሰባት ሱባዔዎች…እና ስድሳ ሁለት ሱባዔዎች

ይሄ የእሥራኤላውያን የሚቆጥሩበት የተለመደ ዓይነት አቆጣጠር አይደለም፡፡“ሰባ ጊዜ ሰባት ዓመታት….ሰባት ጊዜ ሰባት ዓመታት….እና ስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባት ዓመታት”

በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቆጥሯል

እግዚአብሔር የደነገገው በዚህ ጥቅስ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ለሕዝቡና ለእሥራኤል የሚያደርግ መሆኑን ነው፡፡

የአንተ ሕዝብና የአንተ ቅድስት ከተማ

እዚህ ላይ “የአንተ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ዳንኤልን ነው፡፡ሕዝቡ የእሥራኤል ሕዝብ ሲሆን የተቀደሰችው ከተማ ደግሞ ኢየሩሣሌም ናት፡፡

ዓመፃን ይጨርስ በደልንም ያስተሰርይ ዘንድ

ሃሣቡ የተደጋገመበት ምክኒያት ይሄ ነገር በእርግጥ የሚከናወን መሆኑን አፅንዖት ለመሥጠት ነው፡፡

ራዕይን ተሸክሞ መሄድ

እዚህ ላይ “ተሸክሞ መሄድ”የሚለው ቃል ዘይቤያዊ አገላለፅ ሲሆን ትርጉሙ መፈፀም ማለት ነው፡፡“ራዕዩን ተግባራዊ ማድረግ”

ራዕዩና ትንቢቱ

ከዚህ አውድ አንፃር እነዚህ ቃላት ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡ለዳንኤ የሚያረጋግጡት ነገር ቢኖር የኤርምያስ ራዕይ በእርግጥም ትንቢት የነበረ መሆኑን ነው፡፡

ማወቅና ማስተዋል

እነዚህ ቃላት በአንድነት ጥቅም ላይ የዋሉት ጣሚነቱን የበለጠ ግልፅ ለማድረስ ነው፡፡“በግልፅ ልትረዳው ያስፈልጋል”

የተቀባ

መቀባት አንድ ሰው መመረጡ የሚታወቅበት ምልክት ነው፡፡“እግዚአብሔር የሚቀባው ሰው”

ሰባ ሱባዔዎች…እና ስድሣ ሁለት ሱባዔዎች

እነዚህ ሲደመሩ 69 የሚሆኑ ሲሆን በቁጥር 24 ላይ ከተጠቀሱት 70ዎቹ ውስጥ ናቸው፡፡

ኢየሩሣሌም ትሰራለች

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሰዎች ኢየሩሣሌምን እንደገና ይሠሯታል፡፡”

የምሽግ ጉድጓድ

በከተማ ወይም በሕንፃ ዙሪያ ያለና ብዙ ጊዜ ውኃ ያለበት ጥልቅ ጉድጓድ

የጭንቀት ዘመን

“ታላቅ ችግር ያለበት ዘመን”