am_tn/dan/09/20.md

1.1 KiB

ሕዝቤ እሥራኤል

“ወገኔ የሆነው የእሥራኤል ሕዝብ”

የእግዚአብሔር የተቀደሰ ተራራ

ተራራዎቹ የተቀደሱ የሚሆኑት በቤተ መቅደሱ ምክኒያት ሊሆን ይችላል፡፡“የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ያለበት ተራራ”

ሰው የሆነው ገብርኤል

የሰው መልክ ይዞ በትንቢተ ዳንኤል18፡16 ላይ የተገለጠውም ራሱ መልአኩ ገብርኤል ነው፡፡“ሰው መስሎ የተገለጠው ገብርኤል”

አስቀድሜ በራዕይ ያየሁት

ይሄ ዳንኤል ነቅቶ እያለ የተመለከተው የመጀመሪያው ራዕይን የሚመለከት ሊሆን ይችላል፡፡“ከዚህ በፊት በነበረው ራዕይ”ወይም “የቀደመው ራዕይ”

እየበረረ ወደ እኔ መጣ

“በፍጥነት ወደ እኔ እየበረረ መጣ”

በማታ መሥዋዕት ጊዜ

አይሁድ ሕዝቦች ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት በየምሽቱ ለእግዚብሔር መሥዋዕትን ያቀርቡ ነበር፡፡