am_tn/dan/09/17.md

2.3 KiB

አሁን

እዚህ ላይ “በአሁኗ ደቂቃ”ማለት ሣይሆን የሚቀጥለው የዳንኤል የፀሎት ምዕራፍ ሊጀመር ስለመሆኑ የማሳያ መንገድ ነው፡፡

ባሪያህ…ስለ ምሕረት የሚለምነውን የእርሱን ልመና

“ባሪያህ” እና “የእርሱ”የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ዳንኤልን ነው፡፡እግዚአብሔርን ስለማክበሩ እንደ ምልክት ይሆን ዘንድ ስራሱ በሶስተኛ መደብነት(ሰዋሰው)ይናገራል፡፡

ልመናና ምሕረት

“ስለ ምሕረት መለመን”

ፊትሀን አብራ

ፀሐፊው እገዛ በማድረጉ የእግዚአብሔር ፊት እንደ ብርሀን እንዳበራ በሚመስል መልኩ ይናገራል፡፡ “በቅንነት እገዛ ማድረግ” ወይም “ማድላት”

መቅደስህ

ይሄ የሚያመለክተው በኢየሩሣሌም ያለውን ቤተመቅደስ ነው፡፡

ጆሮሀን አዘንብለህ ስማ

“ጆሮን ማዘንበል”የሚለው ቃል ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን ማዳመጥ ማለት ነው፡፡እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ዳንኤል ለሚፀልየው ፀሎት እግዚአብሔር ትኩረት እንዲሰጠው ላለው ፍላጎት አፅንዖት ይሰጡታል፡፡“እባክህን ስማ“

ዓይንህን ገልጠህ ተመልከት

“ዓይን መግለጥ” የሚለው ቃል ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን ማየት ማለት ነው፡፡“ዓይንን መግለጥ”ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን ማዳመጥ ማለት ነው፡፡እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ዳንኤል ለሚፀልየው ፀሎት እግዚአብሔር ትኩረት እንዲሰጠው ላለው ፍላጎት አፅንዖት ይሰጡታል፡፡“አስበን”ወይም “ተመልከት”

ሥምህ ተጠርቶባታል

እዚህ ላይ“ሥም”የሚወክለው ባለቤት መሆንን ነው፡፡“የአንተ ከተማ ናት” ወይም “አንተ ንብረት ናት”

አትዘግይ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በፍጥነት ወደ ተግባር ግባ”