am_tn/dan/09/15.md

1.6 KiB

ኃያል በሆነ እጅ

እዚህ ላይ “ኃያል እጅ”የሚለው ቃል ብርታት ለሚለው ሜቶኒም ነው፡፡

ዛሬም ለራስህ ዝነኛ የሆነ ሥምን አድርገሃል

እነዚህ ሁለት አንቀፆች በመሠረቱ ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን አንድ ላይ እንዲሆኑ የተደረጉት ኃጢአት ምን ያህል ክፉ ነገር እንደሆነ አፅንዖት ይሰጡ ዘንድ ነው፡፡

እኛ ኃጢአትን ሠርተናል፤ክፋትንም አድርገናል

እነዚህ ሁለት አንቀፆች በመሠረቱ ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ቢሆንም “እኛ”የሚለው ቃል እግዚአብሔርን አያካትትም፡፡

ቁጣህና መአትህ

“ቁጣ”እና “መአት”የሚሉት ቃላት በመሠረቱ ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ወደ ድርጊት በሚገባበት ወቅት የእግዚአብሔር ቁጣ ምን ያህል አደገኛ ሊሆን እንደሚችል አፅንዖት ይሰጣል፡፡

የተቀደሰው ተራራህ

ይሄ ተራራ ቅዱስ የሆነበት ምክኒያት እግዚአብሔር መቅደስ እዚያ በመሆኑ ምከኒያት ሊሆን ይችላል፡፡

የእኛ ኃጢአት…አባቶቻችን

እዚህ ላይ“ኃጢአት”የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ሣይሆን ዳንኤልንና እሥራኤልን ነው፡፡

መሰደቢያ

“ለአክብሮት ማጣት ዒላማ”