am_tn/dan/09/07.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ዳንኤል ስለ እሥራኤል ሕዝብ መፀለዩን ይቀጥላል፡፡

ጌታ ሆይ ፅድቅ ለአንተ ነው

እዚህ ላይ ፃድቅ የሚለው ቃል ልክ “ፅድቅ”እግዚአብሔር ባለቤቱ እንደሆነ ዕቃ ተደርጎ ነው፡፡“ፅድቅ” የሚለው አሕፅሮተ ሥም “ፃድቅ”ተብሎ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ጌታ ሆይ አንተ ፃድቅ ነህ”

ለእኛ ዛሬ የፊት ሐፍረት ሆኖብናል…ለሕዝባችን

ሐፍረት የሚለው ቃል እዚህ ሥፍራ ላይ የተገለፀው ልክ“ሐፍረት”ሕዝቡ ባለቤት እንደሆነበት ዕቃ ተደርጎ ነው፡፡“ሐፍረት” የሚለው ተውላጠ ሥም “አፈረ”ተብሎ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እኛን በሚመለከት ግን በሰራነው ሥራ አፍረናል…ሕዝቡ”

ዛሬ ያለነው እኛ

“እኛ”የሚለው ቃል ዳንኤልንና እሥራኤልን የሚያካትት ቢሆንም እግዚአብሔርን ግን አያጠቃልልም፡፡

የፊት ሐፍረት ሆኖብናል

ይሄ ዘይቤያዊ አነጋገር ሐፍረታቸው ለሰው ሁሉ የሚታይ ነው ማለት ነው፡፡

በአንተ ላይ በበደልነው በደል ምክኒያት

“ምክኒያቱም በእጅጉ በድለንሃል” ወይም“ ምክኒያቱም ለአንተ ፈፅሞ ታማኞች አልነበርንም፡፡”