am_tn/dan/09/05.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ዳንኤል ስለ እሥራኤል ሕዝብ መፀለዩን ይቀጥላል፡፡

በድለናል፤ክፋትንም አድርናል

እነዚህ ሁለት ሐረጎች ቃላት አንድ ሃሣብን የሚያንፀባርቁ ቢሆኑም አፅንዖት ለመሥጠት ሲባል በሁለት የተለያዩ መንገዶች ይገልፁታል፡፡

ትዕዛዛትህና ፍርድህ

“ትዕዛዝ”እና “ፍርድ”የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን የሚያመለክቱትም በአጠቃላይ ሕጉን ነው፡፡

ባሪዎችህን አልሰማንም

እዚህ ላይ“አልሰማንም”ማለት መልዕክታቸውን ሰምተን አልታዘዝንም ማለት ነው፡፡“የነቢያቶችህን መልዕክት አልሰማንም”

በስምህ የተናገሩትን

እዚህ ላይ “ሥም”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ሥልጣን ነው፡፡“በሥልጣን የተነገረ” ወይም“አንተን በመወከል የተናገረ”

ለአገሩም ሕዝብ

እዚህ ላይ“አገሩ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው እሥራኤልን ነው፡፡“የእሥራኤል ሕዝብ”