am_tn/dan/08/11.md

1.7 KiB

ሃሣብን ማያያዣ

ዳንኤል ቀንዱን በተመለከተ በራዕይ ያየውን ነገር መግለፁን ይቀጥላል፡፡

አጠቃላይ መረጃ

ቀንዱ የሰው ብቃቶች ተሰጥተውታል፡፡

የሠራዊቱ አለቃ

ይሄ የሚያመለክተው የመላዕክት ሠራዊት አለቃ የሆነውን ራሱን አግዚአብሔርን ነው፡፡

ከእርሱን የተነሳ የዘወትሩ መሥዋዕት ተሻረ

“ተሻረ”ማለት ቀንዱ መሥዋዕት ማቅረቡን አቋረጠ ማለት ነው፡፡እዚህ ላይ “እርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሠራዊት አለቃ የሆነውን እግዚአብሔርን ነው፡፡“ሰዎች በየጊዜው የሚያቀርቡለትን መሥዋዕት እንዲቆም አደረገው፡፡”

የመቅደሱ ሥፍራ ፈረሰ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ቤተመቅደሱን አረከሱት”

የሰማይ ሠራዊት ሲረገጡ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ “ቀንዱ የሰማይ ሠራዊትን ረገጠ”

ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ማታና ጥዋት

ይሄ ምናልባትም ወደ እነዚያ አቅጣጫዎች አመለከተ ማለት ሊሆን ይችላል፡፡እዚህ ላይ“ማታና ጥዋት” አጠቃላይ አነጋገር ሲሆን በመሐል ያሉ ነገሮችን ሁሉ የሚያካትት ማለትም ሙሉ ቀን ወይም ሃያ አራት ሰዓት ማለት ነው፡፡“2,300 የፀሐይ መግቢያዎችና የፀሐይ መውጫዎች”

ከዚያም በኋላ መቅደሱ ይነፃል

“መቅደሱ ነፅቶ ዳግም ወደ ተገቢው ሥርዓቱ ይመለሳል”