am_tn/dan/07/27.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

በዳንኤል ራዕይ ውስጥ የተከሰተው ሰው ለዳንኤል መናገሩን ይቀጥላል፡፡

አጠቃላይ መረጃ

ከቁጥር 23 እስከ 27 ድረስ ያለው አብዛኛው ክፍል ተምሣሌታዊ ቋንቋ ነው፡፡

መንግሥትም ግዛትም ለሕዝብ ይጥ ዘንድ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር መንግሥትንና ግዛትን ለሕዝቡ ይሰጣል፡፡”

መንግሥትና ግዛት

በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ይህም መንግሥታዊ ሥልጣንን ሁሉ የሚመለከት ነው፡፡

የመንግሥቱ ታላቅነት

“ታላቅነት” የሚለው አሕፅሮተ ሥም “ታላቅ” በሚለው ቅፅል ሊተረጎም ይችላል፡፡“ስለ መንግሥታቱ ታላቅ የሆነው ነገር ሁሉ”

ከሰማይም በታች ያሉ መንግሥታት

“ከሰማይ በታች ያሉ ሁሉ” የሚለው ዘይቤያዊ አነጋገር የሚያመለክተው በምድር ላይ የሚገኙትን መንግሥታት ነው፡፡“…..በምድር ላይ ካሉ መንግሥታት መካከል”

መንግሥቱ

“የልዑሉ መንግሥት”

የዘላለም መንግሥት

“ለዘላለም ፀንቶ የሚኖር መንግሥት” ወይም “መጨረሻ የሌለው መንግሥት”

የነገሩም ፍፃሜ እስከዚህ ድረስ ነው

ይሄ ማለት ዳንኤል ራዕዩን ማካፈል አቁሟል ማለት ነው፡፡“በራዕይ ያየሁት ይህንን ነው” ወይም “በራዕይ የተመለከትኩት የመጨረሻው ገለፃዬ እዚህ ላይ ያበቃል”

ፊቴም ተለወጠብኝ

“ፊቴ ገረጣብኝ”