am_tn/dan/07/25.md

2.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ዳንኤል በራዕይ የሚመለከተው ሰው መናገሩን ይቀጥላል፡፡

አጠቃላይ መረጃ

ከቁጥር 23 እስከ 27 ድረስ ያለው አብዛኛው ክፍል ተምሣሌታዊ ቋንቋ ነው፡፡

በልዑልም ላይ ቃልን ይናገራል

ይሄ ማለት አዲሱ ንጉስ ሙሉ በሙሉ የሚቃወምና በልዑሉ ላይ መጥፎ ነገሮችን የሚናገር ነው ማለት ነው፡፡

ቅዱሳን

“የእግዚአብሔር የተቀደሱ ሕዝቦች”

ክብረ በዓላትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ

ሁለቱም ቃላት የሚያመለክቱት የሙሴን ሕግ ነው፡፡በብሉይ ኪዳን ዘመን ክብረ በዓላት የኃይማኖት አስፈላጊ የሆኑ ክፍሎች ነበሩ፡፡

እነዚህ ነገሮች በእጁ ተላልፈው ይሰጣሉ

እዚህ ላይ “በእጁ” የሚለው ቃል በቁጥጥር ሥር ማድረግን የሚያመለክት ነው፡፡ይሄ በገቢር መልክ መገለፅ ይችላል፡፡“አዲሱ ንጉሥ ኃይማኖታዊ ክብረ በዓላትንና ሕጎችን በበላይነት ይቆጣጠራል፡፡”

አንድ ዓመት፤ሁለት ዓመት እና ግማሽ ዓመት

ይሄ “ሶስት ዓመት ተኩል” ማለት ነው፡፡ይሄ እሥራኤላውያን የሚቆጥሩት የተለመደ ዓይነት አቆጣጠር አይደለም፡፡“አንድ ዓመት ሲደመር ሁለት ዓመት ሲደመር ግማሽ ዓመት”

ፍርድም ይሆናል

ይሄ ዳኛው መረጃዎቹን ለመመርመርና ፍርድ ለመስጠት ይዘጋጃል ማለት ነው፡፡“ዳኛው ፍርድን ይፈርዳል” ወይም “ዳኛው ለመፍረድ ይቀመጣል”

መንግሥታዊ ሥልጣኑን ይወስዱበታል

“የፍርድ ቤቱ አባላት ከአዲሱ ንጉስ መንግሥታዊ ሥልጣኑን ይነጥቁታል”

ንጉሣዊ ሥልጣን

አዚህ ላይ ይሄ የሚያመለክተው “ሥልጣንን”ነው፡፡ይሄንን በትንቢተ ዳንኤል 7፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡

እስከ ፍፃሜም ድረስ ያፈርሱትና ያጠፉት ዘንድ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በመጨረሻ ያቃጥሉትና ያጠፉት ዘንድ”ወይም “በመጨረሻም ንጉሣዊ ሥልጣኑን ፈፅሞ ያጠፉታል፡፡”