am_tn/dan/07/23.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ከቁጥር 23 እስከ 27 ድረስ ያለው አብዛኛው ክፍል ተምሣሌታዊ ቋንቋ ነው፡፡

ያ ሰው የተናገረው ይሄንን ነው

ይሄ ሰው በትንቢተ ዳንኤል 7፡16 ላይ ዳንኤል የተገናኘው ነው፡፡

ያ ሰው እንዲህ አለ

“ያ ሰው መለሰ”

ስለ አራተኛው አውሬና…ስለ አሥሩ ቀንዶች

“አራተኛውን አውሬ በተመለከተ…አሥሩን ቀንዶች በተመለከተ”ወይም “አሁን፤ስለ አራተተኛው አውሬ…አሁን፤ስለ አሥሩ ቀንዶች”

ይበላል…ያደቅቃትማል

እዚህ ላይ አራተኛው መንግሥት ዓለምን ያጠፋል ማለት ሣይሆን በጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ያጠቃል፤ድል ያደርጋል እንዲሁም በምድር ላይ የሚገኙትን መንግሥታት ሁሉ ያጠፋል ማለት ነው፡፡

ከዚህ መንግሥት አሥር ነገሥታት ይነሣሉ

አንዱ ሌላው እየተካ ይገዛሉ፡፡ይሄ ግልፅ በሆነ መልኩ ሊገለፅ ይችላል::”ከዚህ ከአራተኛው መንግሥት በላይ አስር ነገስታት በመከታተል ይነግሳሉ፡፡”

ከእነርሱም በኋላ ሌላ ይነሳል

ይሄ ንጉሥ ከአስሩ መካከል አይደለም፡፡ምናልባትም እርሱን “አስራ አንደኛው ንጉሥ”ማለቱ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡“ከዚያ በመቀጠል አስራ አንደናው ንጉሥ ኃያል እየሆነ ይመጣል”

ከፊተኞቹ የተለየ ይሆናል

“ከሌሎቹ አስር ነገሥታት የተለየ ይሆናል፡፡”