am_tn/dan/07/13.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

አብዛኛዎቹ ከቁጥር 9 እስከ 14 ድረስ ያሉት ክፍሎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ተምሣሌታዊ አነጋገሮች ናቸው፡፡ከዚህ የተነሣ ሌሎች ቅጂዎች በቅኔያዊ ዘይቤ ያቀርቧቸዋል፡፡

አንዱ ሲመጣ ተመለከትኩ…የሰው ልጅ የሚመስል

ዳንኤል የተመለከተው ሰው የተለመደው ዓይነት ሰው አይደለም፡፤ነገር ግን የሰው ዓይነት ቅርፅ ነበረው፡፡“በዚያን ሌሊት የሰው ልጅ የሚመስል ሲመጣ ተመለከትኩ፡፡ማለትም የሰው ምስል ነበረው”

ከሰማይ ደመናት ጋር

“በሰማይ ላይ ካሉ ደመናት ጋር”

እስከ ዘመንና ጊዜ ድረስ

ይሄ የሚያመለክተው ዘላለማዊ የሆነውን እግዚአብሔርን ነው፡፡ይህንን በትንቢተ ዳንኤል 7፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡

ወደ ፊቱም አቀረቡት

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ለዘላለም በሸመገለው ፊት አቀረቡት” ወይም “በፊቱ ቀረበ”

ግዛትና ክብር መንግሥትም “lk” ተሰጠው

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የሰው ልጅ የሚመስለው ለመግዛት፤ክብርና መንግሥታዊ ሥልጣን ተሰጠው፡፡”

የመንግሥት ሥልጣን

እዚህ ላይ ይሄ የሚያመለክተው “ሥልጣንን” ነው፡፡

ወገኖች፤አህዛብና ቋንቋዎች

እዚህ ላይ “አህዛብ”እና “ቋንቋ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ የተለያዩ ወገኖችን ነው፡፡ይህንን በትንቢተ ዳንኤል 3፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመለከቱ፡፡

የዘላለም ነው …በፍፁም የማይጠፋ ነው

እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡