am_tn/dan/07/11.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ዳንኤል በሰማይ የሚካሄደውን ፍርድ በሚመለከት የተመለከተውን ራዕይና በትንቢተ ዳንኤል 17፡7 ላይ ስለተመለከተው አራተኛው እንስሳ የሚሰጠውን መልስ በሚመለከት ገለፃ ማድረጉን ይቀጥላል፡፡

አውሬው ተገደለ…እስኪቃጠል ድረስ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“አራተኛውን አውሬ ገደሉት፤አካሉን አጠፉ፤እንዲያቃጥለውም ለሆነ ሰው ሰጡት”

አውሬው ተገደለ

አውሬው የእንዲገደል የተደረገበት ምክኒያት ዳኛው ጥፋተኛ መሆኑን በመወሰኑ ነው፡፡ “አውሬውን አረዱት”ወይም “ዳኛው ውሳኔውን ካስተላለፈ በኋላ አውሬውን ገደሉት”

አውሬው

ይሄ የሚያመለክተው አስር ቀንዶች ስለነበሩትና በትዕቢት ይናገር ስለነበረው አውሬ ነው፡፡“እጅግ አስፈሪ የሆነ አውሬ”ወይም “በትዕቢት የተወጠረ ቀንዶች ያሉት”

የቀሩት አራቱ አውሬዎች

“የቀሩት ሶስቱ አውሬዎች” ቢባል የበለጠ ግልፅ ይሆናል፡፡

ግዛታቸውም ተወሰደ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ዳኛው የመግዛት ሥልጣናቸውን ነጠቃቸው” ወይም “የገዢነታቸው ዘመን ተጠናቀቀ”

የሕይወታቸው ዕድሜ እስከ ዘመንና ዘመን ድረስ ተራዘመ

x