am_tn/dan/07/10.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ዳንኤል በሰማይ የሚካሄደውን ፍርድ በሚመለከት የተመለከተውን ራዕይና በትንቢተ ዳንኤል 17፡7 ላይ ስለተመለከተው አራተኛው እንስሳ የሚሰጠውን መልስ በሚመለከት ገለፃ ማድረጉን ይቀጥላል፡፡

አጠቃላይ መረጃ

ከቁጥር 9 እስከ 14 ውስጥ የሚገኘው ክፍል ተመሳሳይ ትርጉምና ተምሣሌታዊ ቋንቋ ያለው ናቸው፡፡ከዚህ የተነሣ አንዳንድ ቅጂዎች በቅኔያዊ ዘይቤ እንዲቀርብ አድርገውታል፡፡

የውኃ ፈሳሽም ከፊቱ ይወጣ ነበር

ከእግዚአብሔር ፊት እሣቱ በፍጥነት የመውጣቱን ነገር ልክ እሣት ያለበት ወንዝ እንደሚፈስስ ዓይነት ተደርጎ ቀርቧል፡፡“ልክ በወንዝ ውስጥ እንዳለ ውኃ እሣት ከፊቱ ወጣ”

በፊቱ

“በፊቱ” ቃል የሚያመለክተው ራሱን እግዚአብሔርን ነው፡፡በትንቢተ ዳንኤል 7፡9 ላይ ከዘመናት በፊት የሚለውን ይመልከቱ፡፡

ሚሊዮኖች

ይሄ ምናልባት የሚያመለክተው የተወሰነ ቁጥርን ሣይሆን ትልቅ ቁጥር ያለውን ሕዝብ ሊሆን ይችላል፡፡ “እልፍ አዕላፋት” ወይም “10 ሺዎች ጊዜ አሥር ሺዎች” ወይም “ለመቁጠር የሚያዳግቱ ሕዝቦች”

ፍርድም ሆነ

ይሄ ማለት ፈራጅ የሆነው እግዚአብሔር ማሰረጃውን ለማጤንና ፍርድ ለመሥጠት ተዘጋጅቷል ማለት ነው፡፡“ፈራጁ ፍርድን ለመሥጠት ተዘጋጅቶ ነበር”ወይም “ዳኛው ተቀምጦ ነበር”

መፃሕፍትም ተገለጡ

እነዚህ መፃሕፍት በፍርድ ዙፋኑ ፊት ጠቃሚ ሆኑ ማስረጃዎችን የያዙ ናቸው፡፡“ማስረጃ የያዙት መፃሕፍት ተከፈቱ”