am_tn/dan/07/09.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

አብዛኛዎቹ ከቁጥር 9 እስከ 14 ድረስ ያሉት ክፍሎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ተምሣሌታዊ አነጋገሮች ናቸው፡፡ከዚህ የተነሣ ሌሎች ቅጂዎች በቅኔያዊ ዘይቤ ያቀርቧቸዋል፡፡

ዙፋኖች ተዘረጉ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የሆነ ሰው ዙፋኖቹን በየሥፍራቸው አስቀመጣቸው፡፡”

በዘመናት መካከል

ይሄ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ሥም ሲሆን ለዘላለም የሚኖር ነው የሚል ፍቺ ያለው ነው፡፡“ለዘላለም የኖረው”ወይም “ዘወትር ሕያው የሆነው”

ተቀመጠ…ልብሱ…የራሱም ጸጉር

ይሄ ዓረፍተ ነገር እግዚአብሔርን ልክ እንደ ሰው ልብስ ለብሶ እንደሚቀመጥ ዓይነት አድርጎ ይገልፀዋል፡፡እግዚአብሔር እንደዚህ ነው ማለት ሣይሆን ዳንኤል እግዚአብሔርን በራዕይ ያየው በዚህ መልኩ ነበር፡፡