am_tn/dan/07/04.md

1.5 KiB

መጀመሪያይቱ አንበሣ ትመስል ነበር የንስርም ክንፍ ነበራት

ይሄ ተምሣሌታዊ ፍጥረት እንጂ በምድር ላይ የሚኖር የእንስሳ ዘር አይደለም፡፡

ክንፎችዋም ከእርስዋ እስኪነቀሉ ድረስ አይ ነበር፤ከምድርም ከፍ ከፍ ተደረገች፤እንደ ሰውም በሁለት እግር እንድትቆም ተደረገች

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ “የሆነ ሰው ክንፎችዋን ነቅሎ ከምድር ላይ ካነሳት በኋላ ልክ እንደ ሰዎች በሁለት እግሮቿ እንድትቆም አደረጋት፡፡”

የሰውም ልብ ተሰጠው

እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አስተሳሰብን ነው፡፡ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የሆነ ሰው እንደ ሰው የማሰብ ችሎታ እንዲኖራት አደረገ”

ሁለተኛው እንሥሳ…አንደ ድብ

ይሄ በገሃዱ ዓለም የሚገኝ እንስሳ አይደለም፡፡ከድብ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ተምሳሌታዊ አንስሳ ነው፡፡

የጎድን አጥንት

ከጀርባ የአጥንት አከርካሪ ጋር የሚገናኙ ሠፊና ጠምዛዛ የሆኑ የደረት አጥንቶች ናቸው፡፡

ተባለላት

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የሆነ ሰው ተናገረው”