am_tn/dan/06/24.md

1.6 KiB

የአንበሶች ጉድጓድ

ይሄ አንበሶች ተጠብቀው የሚኖሩበትን ክፍል ወይም ጉድጓድ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል፡፡ይህንን በትንቢተ ዳንኤል 6፡7 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡

ወደ ጉድጓዱ መጨረሻ ሳይደርሱ

“በአንበሶቹ ጉድጓድ ወለል ላይ ከመድረሳቸው በፊት”

አጥንታቸውንም ሰባበሩ

“አጥንታቸውን አደቀቁት”

ወገኖች፤አህዛብና ቋንቋዎች

እዚህ ላይ “አህዛብ” እና “ቋንቋዎች”የሚለው ቃል የሚወክለው ከተለያዩ ነገዶች የመጡና የተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ሰዎችን ነው፡፡ይህንን በትንቢተ ዳንኤል 6፡7 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ “ከተለያዩ ነገዶች የመጡና የተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ሰዎች”

በምድር ሁሉ

ንጉሥ ዳርዮስ መልክዕቱን የፃፈው ሠፊ ለነበረው ግዛቱ ሁሉ ነበር፡፡ምንም አንኳን በምድር ላይ የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ የሚያጠቃልል ባይሆንም እዚህ ላይ “በምድር ሁሉ”የሚለው ቃል መንግሥቱ ምን ያህል ሠፊ እንደነበረ አፅንዖት ለመሥጠት ነው፡፡“በመንግሥቱ ውስጥ”

ሰላም ይብዘላችሁ

ይሄ በሁሉም የሕይወት ዘርፎች ለአንድ ሰው መለካም ይሆንለት ዘንድ ለመመኘት የሚቀርብ የሠላምታ ዓይነት ነው፡፡