am_tn/dan/06/17.md

1.7 KiB

X

ይሄ አንበሶች ተጠብቀው የሚኖሩበትን ክፍል ወይም ጉድጓድ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል፡፡ይህንን በትንቢተ ዳንኤል 6፡7 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡

ንጉሱም በዳንኤል ላይ የተደረገው እንዳይለወጥ በቀለበቱና በመኳንንቱ ቀለበት አተመው

በቀለበት የመታተሙ ጠቀሜታ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡ንጉሱና መኳንንቱ በሰም በተሰራ ማህተም በቀለበታቸው አተሙት፡፡ንጉሱ ፊርማውን በሰም ውስጥ አድርጎ ካተመ በኋላ መኳንንቶቹም በተመሳሳይ ሁኔታ አደረጉ፡፡ማንም ሰው ቢሆን ዳንኤልን ለመርዳት በሚል ሰበብ ማሕተሙ ያዘለውን ትዕዛዝ ለመሻር አልተፈቀደለትም ነበር፡፡

በዳንኤል ላይ የተወሰነው ነገር እንዳይለወጥ

“ማንም ሰው ቢሆን ዳንኤልን ለማገዝ አይችልም ነበር”

ሳይበላም አደረ

ይህ ድርጊት የሚያሣየው ንጉሱ የዳንኤል ጉዳይ ምን ያህሰል ያስጨነቀው መሆኑን ነው፡፡

የሚያዝናኑ ነገሮች በፊቱአልቀረቡለትም

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የሚያዝናናው ማንም ሰው አልነበረም”

እንቅልፍም ከእርሱ ራቀ

እንቅልፍ ልክ ከንጉሱ እየሮጠ እንደሚሄድ ዓይነት ነገር ነው የተገለፀው፡፡“በዚያን ሌሊት ሁሉ እንቅልፍ ሳይዘው አሳለፈ”